የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር MSF/LP/05/2020
በስኳር ኮርፖሬሽን የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ጥቅል አንድ፡- ኤሌክትሮድ (Electrode)
- ጥቅል ሁለት፡- ቤሪንግ (Bearing)
- ጥቅል ሶስት፡- ሰንሰለት (Chain)
- ጥቅል አራት፡ የተለያዩ ብርታብረቶች እና የጋራዥ ለጠቅላላ አገልግሎት (Square Pipe Sheet Metal, RHS, Steel Beam, Round Steel & General Use FEM)
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ፤የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመስስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሠዓት ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220 የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሠርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቢያንስ 2% በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.ኢ.አ.. ሐምሌ 16 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4:00 ሠዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 119 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዕለቱ ሐምሌ 16 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡-0115-505607
0115-505821
ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ አዲስ አበባ
በስኳር ኮርፖሬሽን የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ