በስኳር ኮርፖሬሽን አርጆ ዴዴሳ ስኳር ፋብሪካ: የተጨፈላለቁ ብረታብረቶች መሸጥ ይፈልጋል።

አዴስፋ/ልጨ/002/2011

በስኳር ኮርፖሬሽን አርጆ ዴዴሳ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን በፋብሪካው ቅጥር ግቢ የሚገኙ ለብረታ ብረት ፋብሪካና ለሌሎችም ተመሳሳይ ድርጅቶች ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

 • የተጨፈላለቁ ብረቶች፤ ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎችና በርሜሎች፣ ቁርጥራጭ ብረታብረቶች፤ ቫልቮች፤የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌትሪክ ሽቦዎች ወዘተ
 • የብረት በርሚሎች

ስለሆነም:-

በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው አካላት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀናት ድረስ በፋብሪካው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አዲስ አበባ ፊሊፕስ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402A ቀርበው ለዚህ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

 1. ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (Tin No.)ያላቸው፤
 2. በሚወዳደሩበት ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ለዚህም አግባብ ካለው የመንግስት መ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ፤
 4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በእያንዳንዱ በጨረታ ሰነዱ መሠረት እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
 5. ጨረታው በታሸገ ፖስታ መቅረብ ያለበት ሲሆን የአስፈላጊ ሰነዶች ትክክለኛ ኮፒ እና ሲፒኦ አብሮ መታሸግ አለበት።
 6. ጨረታው በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሊገኙ ፈቃደኛ በሆኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
 7. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ነገሮች ማሻሻል ወይም መተው አይችልም።
 8. በጨረታው የሚሳተፉ አቅራቢዎች ከዚህ በላይ የተገለፁትን በአግባቡ ሳይፈፅሙ ቢቀሩ ለጨረታ ማስረከቢያ የተያዘው ገንዘብ ለፋብሪካው ገቢ ሆኖ ተጫራቹ ከጨረታው ይሰረዛል።
 9. ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ፡አርጆ ዴዴሳ ስኳር ፋብሪካ ሜክሲኮ ሊፕስ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 406 የስልክ ቁጥር፡- 0115586073/0912102506) አዲስ አበባ በመደወል ወይም ዘወትር በሥራ ሰዓት በግንባር በመቅረብ ማነጋገር ይቻላል።
 10. ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ