ግልፅ ያጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አዲስሩ ግጨ/022/ 2012 ዓ.ም
በስኳር ኮርፖሬሽን አርጆ ደዴሳ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ለፋብሪካ አግልግሎት የሚውሉ በሎት 01 የተጠቀሱትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እንዲሁም በሎት 02 የተጠቀሰውን ከጨረታ አሸናፊ ጋር አወዳድሮ በየአመቱ የሚታደስ ውል መፈራረም ይፈልጋል፡፡
- ሎት 01-የተለያዩ የፋብሪካ የኤሌክትሪክ መሣሪያዎች እና መለዋወጫዎች
- ሎት 02- ሀይድሮሊክ ሆዝ መጭመቅ
ስለሆነም በጨረታ ለመወዳደር ፍላጎት ያላችሁ አካላት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ6 ቀናት በፋብሪካ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት አዲስ አበባ ፊሊፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 ቀርበው ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳዱ ሎት ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN NO.)
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሎት 01 ብር 5000 /አምስት ሺህ/ እና ለሎት 10,000 /አስር ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ማቅርብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ ለየብቻው ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን በኋላ 8፡30 ሊገኙ ፈቃደኛ በሆኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ነገሮች ማሻሻል ወይም መተው አይችልም፡፡
- በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቾች ከዚህ በላይ የተገለፁትን በአግባቡ ሳይፈፅሙ ቢቀሩ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለፋብሪካው ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ለማግኝት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ፡
አርጆ ደዴሳ ስኳር ፋብሪካ
ሜክሲኮ ፊሊፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215
የስልክ ቁጥር 0115586073/0912-10-2506
አዲስ አበባ
በመደወል ወይም ዘወትር በሥራ ስዓት በግንባር በመቅረብ ማነጋገር ይቻላል፡፡
10. ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በስኳር ኮርፖሬሽን የአርጆ
ደዴሳ ስኳር ፋብሪካ