Building Construction / Contract Administration and Supervision

በሲዳማ ዞን የይርጋ ዓለም አጠቃላይ ሆስፒታል በ2012 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው የባለ ሁለት ወለል( G+2) የዶክተሮች ማደሪያ ህንፃ ማጠናቀቂያ ግንባታ ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 3/2012 ዓ/ም 

በሲዳማ ዞን የይርጋ ዓለም አጠቃላይ ሆስፒታል በ2012 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው የባለ ሁለት ወለል( G+2) የዶክተሮች ማደሪያ ህንፃ ማጠናቀቂያ ግንባታ ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ 

 1.  ደረጃቸው GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራቾች 2012 ዓ.ም ፍቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin No/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይንም አግባብነት ካለው መንግስት ተቋም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
 2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶች በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡
 3. በሲዳማ ዞን ውስጥ ከ2009 ዓ.ም እና ከዚያ በፊት ፕሮጀክቶችን ከአሰር እና ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤት ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በወቅቱ ፕሮጀክቱ የዘገየበት ገላጭ ምክንያት ከአሠሪ መሥሪያ ቤት እና ከሚመለከታቸው አካላት የፀደቀ እና በሰነድ የተደገፈ መረጃ ካለ በስተቀር የውል ጊዜ ያለፈባቸውንና ያላስረከቡ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡ 
 4. በሲዳማ ዞን ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሰር እና ከሚመለከታቸው መ/ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በወቅቱ ፕሮጀክቱ የዘገየበት ገላጭ ምክንያት ከአሠሪ መ/ቤት እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የፀደቀ እና በሰነድ የተደገፈ መረጃ ካለ በስተቀር መልካም ሥራኤፈፃፀም የሌላቸው ተቋራጮች ጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡ 
 5. የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና ኦርጅናል ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፣ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሣክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
 6. የጨረታ ማስከበሪያ Bid Security/ ብር 90,000.00 /ዘጠና ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይንም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡ 
 7. የሥራ ተቋራጮች ሰተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፍቃዳቸውንና ተፈታ VAT| የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት እና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 በሃያ አንድ ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ ይርጋ ዓለም አጠቃላይ ሆስፒታል ፋይናንስ ክፍል በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ 
 8. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በእራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ 
 9. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond security/ ፋይናንሻል አንድ ዋና ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽገው በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተው እና በሁሉም ዶክመንት ላይ ሥም እና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታትይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22 በሃያ ሁለተኛው ቀን ከጠዋቱ 4 እስከ 6 ሰዓት በይርጋ ዓለም አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡ 
 10. በጨረታ አከፋፈት ሥነ ሥርዓት ላይ የተነበበው ጠቅላላ ዋጋየሂሳብ ስህተት Arethmetic Check/ ማስተካከያ በሚደረግበት ጊዜ የመጣው የሂሳብ ልዩነት /Arethemetec Error/ ከጠቅላላ ሁለት ከመቶ በላይ መጠን የሚበልጥ ወይንም ሁለት ከመቶ የሚያንስ ከሆነ ሥራ ተቋራጩ በቀጥታ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ 
 11. ተጫራቹ የሚሞላው ሪቪት አስር ከመቶ እና ከዚያ በታች መሆን አለበት፡፡ ከአስር በመቶ በላይ ሪቨት ያስገቡ ተጫራቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ያስገባው ዋጋ ውድቅ ሆኖ ከጨረታው ውጭ ይሆናል
 12. በተሻሻለው የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት የግዥ አዋጅ መሠረት የግንባታ ሥራውን ለማሰራት በቅድሚያ ከተገመተው አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋ /Enginering Estimation/ ከአስራ አምስት ከመቶ በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይንም የሚያንስ ከሆነ የሥራ ተቋራጩ ቀጥታ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ 
 13. ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ቦታ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 /ስምንት ሰዓት) ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቶቹ አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም፡፡ 
 14. አሰሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 15. የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ 

በሲዳማ ዞን የይርጋ ዓለም አጠቃላይ ሆስፒታል