Building Construction / Finishig Works / House and Building

በሲዳማ ዞን ቦና ዲስትሪክት ሆስፒታል በ2012 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው የባለ ሁለት ወለል (G+2) የቢሮ ሕንፃ ቀሪ ሥራ ግንባታ ሥራ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ 

በሲዳማ ዞን ቦና ዲስትሪክት ሆስፒታል በ2012 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው የባለ ሁለት ወለል (G+2) የቢሮ ሕንፃ ቀሪ ሥራ ግንባታ ሥራ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። 

በዚሁ መሠረት፦ 

 1. ደረጃቸው GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራቾች 2012 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም አግባብነት ካለው መንግሥት ተቋም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ 
 2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርስው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡ 
 3. በሲዳማ ዞን ውስጥ ከ2009 ዓ.ም እና ከዚያ በፊት ፕሮጀክቶችን ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤት ጋር ሕጋዊ ውል ገብተው በወቅቱ ፕሮጀክቱ የዘገየበት ገላጭ ምከንያት ከአሠሪ መሥሪያ ቤት እና ከሚመለከታቸው አካላት የፀደቀና በሰነድ የተደገፈ መረጃ ካለ በስተቀር የውል ጊዜ ያለፈባቸውና ያላስረከቡ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም፣ 
 4. በሲዳማ ዞን ውስጥ ፕሮጀከቶችን ሰርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ሕጋዊ ውል ገብተው በወቅቱ ፕሮጀከቱ የዘገየበት ገላጭ ምከንያት ከአሠሪ መሥሪያ ቤት እና ከሚመለከታቸው አካላት የፀደቀና በሰነድ የተደገፈ መረጃ ካለ በስተቀር መልካም ሥራ አፈፃፀም የሌላቸው ተቋራጮች ጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፣ 
 5. የሥራተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት(ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦርጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው። ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጪ ይሆናል። 
 6. የጨረታ ማከበሪያ (Bid Security)ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ(CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም። 
 7. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቶች መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፈቃዳቸውንና ተዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር)ቦና ዲስትሪክት ሆስፒታል ፋይናንስ ክፍል በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ : 
 8. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ ይችላሉ:: 
 9. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (Bid bond/security) ፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በቦና ዲስትሪክት ሆስፒታል ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሽግ አለበት። 
 10. በጨረታ አከፋፈት ሥነ-ሥርዓት ላይ የተነበበው ጠቅላላ ዋጋየሂሳብ ስህተት (Arthimetic Check) ማስተካከያ በሚደረግበት ጊዜ የመጣው የሂሳብ ልዩነት (Arthimetic Error) ከጠቅላላ ዋጋ ከ2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም ከ 2% የሚያንስ ከሆነ ሥራ ተቋራጩ በቀጥታ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናል። 
 11. ተጫራቹ የሚሞላው ሪሴት 10% እና ከዚያ በታች መሆን አለበት። ከ10% በላይ ሪቤት ያስገባ ተጫራች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ያስገባው ዋጋ ውድቅ ሆኖ ከጨረታው ውጪ ይሆናል። 
 12. በተሻሻለው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ መንግሥት የግዥ አዋጅ መሠረት የግንባታ ሥራውን ለማሠራት በቅድሚያ ከተገመተው አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋ Egineering Estimation) ከ5% (ከእሥራ አምስት በመቶ) በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ የሥራ ተቋራጩ ቀጥታ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናል:: 
 13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቶች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም። 
 14. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
 15. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል። 

ቦና ዲስትሪክት ሆስፒታል 

ቦና