የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት የጭሬ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች
- አላቂ የቢሮ ዕቃ /ስቴሽነር/ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ዕቃ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች በሙሉ እንድሳተፉ እንጋብዛለን፡፡
- በዘርፉ ቀጥተኛ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ ያለው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፍቃዳቸውን በበጀት ዓመቱ ያሳደሱ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዘጋቢ የሆኑና ወረሐዊ (VAT) ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለአቅራቢነት የተመዘገቡና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 6,000 /ስድስት ሺህ/ብር የጭሬ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፕኦ /CPO/ በማሰራት ማስገባት የሚችሉ፡፡
- አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በቂ ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በገባው ውል መሠረት ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ ዕቃ ማቅረብና ቅድመ ናሙና ማሳየት የሚችል ተጫራች ለጨረታ የተዘጋጀው ሰነድ በሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት ፋ/ኢ/ል/ቢሮ ግቢ ውስጥ በቢሮ ቁጥር 42 ወረዳውን ወክሎ ሰነዱን ከያዘው ባለሙያ እጅ በብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመግዛት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 17 ቀናት በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችል መሆኑን እያሳወቅን በ17ኛው ቀን ከጠዋቱ በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ በቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ላይ ህጋዊ ማህተም በሰም የታሸገ ፖስታ እንድታስገቡ እናሳስባለን፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ዕቃዎች በትክክል የጥራት ደረጃ የጠበቀ ዕቃ በማቅረብ ሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት ፋ/ኢ/ል/ቢሮ ድረስ ማስረከባቸው እደተረጋገጠ ክፍያው ወዲያ ይፈጽማል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን የሚከፈትበትን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 09 10 74 06 70/09 11 26 57 40/ 09 94 37 12 90/ 09 32 32 05 05
በሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት የጭሬ
ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት