ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2013 የቢሮ ሼልፍ ግዥ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የቢሮ ሸልፍ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፦
ተ/ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
ምርመራ |
1 |
የቢሮ ሸልፍ ግዥ |
በቁጥር |
9 |
ስለ ቢሮ ሸልፍ ዝርዝር ቴክኒካል መረጃ በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኙታል |
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ እና ሌሎች ያሏቸውን ማስረጃዎቻቸውን በግልጽ ሊነበብ በሚችል መልኩ አደራጅተው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ሎጊታ ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሮ ሀዋሳ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ /ፕሮፎርማ/ ፋይናንሻል ዶክመንት ኮፒና ኦርጅናል በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 12ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ሎጊታ ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሮ ሀዋሳ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ12ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ /ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ሎጊታ ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሮ ሀዋሳ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ ከጠቅላላው የግዥ መጠን (ብዛት) ላይ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ። ነገር ግን የጨረታው ሳጥን የሚታሸግበት እና የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ባይሆን የጨረታው ሳጥን የማሸጉም ሆነ የመከፍቱ ሥነ-ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ