የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በይርጋለም ከተማ የሚገኘው ፉራ የልማት ጥናትና ት/ት ተቋም አ.ማ. የ2012 በጀት ዓመት (ሥራ ዘመን) የሂሳብ ኦዲት ሥራ (Financial Audit Work) በገለልተኛ ኦዲት ድርጅት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል:: ስለሆነም ከዚህ በታች
የተገለፁ መስፈርቶችን ሊያሟላ የሚችል ገለልተኛ ኦዲት ድርጅት መወዳደር ይችላል::
- በዘርፉ የታጀለ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፤
- የግብር መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ሰርተፍኬት ከታደሰው ንግድ ፈቃድ ጋር ማቅረብ የሚችል፤
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችል፣
- ተጫራች ለአንዱ ሠነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ በይርጋለም እና ሃዋሳ ካምፖስ በሚገኙ ገ/ያገርች መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጥንቃቄ በማሸግ፤ ይህ ማስታቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ 15ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ድረስ ይርጋለም በሚገኘው ዋና ግቢ በፀሐፊ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው በዕለቱ ከቀኑ (ከሰዓት) 8፡30 ተጫራች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይርጋለም ዋና ግቢ አዳራሽ ቁጥር 2 ይከፈታል::
ማሳሰቢያ፡-
- ጨረታ ማስገቢያ እና የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል::
- በተጨማሪም መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፤- 0462250249/0462250250/0462250604 ይርጋለም 0462203348 ህዋሳ