Others / Road and Bridge Construction

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ይርጋ ዓለም ሆስፒታል በ2013 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው የአስፓልት ጥገና ሥራ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

 የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2/2013 /

 

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ይርጋ ዓለም ሆስፒታል 2013 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው የአስፓልት ጥገና ሥራ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

 1. ደረጃቸው GC-5/RC-4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራቾች 2012 . ፍቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin No./ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይንም አግባብነት ካለው መንግስት ተቋም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
 2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎችን ሀብቶች በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡
 3. ሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት ቴክኒክ/ መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና /ኦርጅናል/ ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፣ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሣክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
 4. የጨረታ ማስከበሪያ Bid Security/ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /Bank GAURANTEE/ ወይንም የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል  ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይንም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
 5. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፍቃዳቸውንና ተእታ /VAT/የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት እና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ 30 ሰላሳ/ ተከታታይ ቀናት ማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ ይርጋ ለም አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥ ከፍያ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 6. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት ሰእራሳቸው ወጭ አይተው ማረጋገጥ ይችላሉ
 7. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond security/ ፋይናንሻል አንድ ዋና ኦርጅናል/ እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና ኦርጅናል/ እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽገው በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተው እና በሁሉም ዶክመንት ላይ ሥም እና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 31 /ሰላሳ አንደኛው/ ቀን ከጠዋቱ 4 እስከ 6 ሰዓት በይርጋ ዓለም አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 4 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
 8. ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ቦታ ከቀ ስድስት  ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8.00 /ስምንት ሰዓት/ ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቶቹ አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
 9. አሰሪው /ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ አይገደድም፡፡
 10. አሸናፊው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 11. የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ይርጋ

ዓለም አጠቃላይ ሆስፒታል