የማሽን ኪራይ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በ2013 በጀት ዓመት በሰ/ሸዋ ዞን ኣንኮበር ወረዳ የአልዩ አምባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በከተማ ውስጥ ለውስጥ መንገድ ለመክፈት
ስለፈለገ ለዚህ ስራ የሚያስፈልጉ ማሽኖች ማለትም፡-
- የማሽኑ አይነት ዶዘር ብዛት አንድ መለያ ሞዴል በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኝ ስሪቱ 2012 እኤአ የሆነ በላይ ለስራው የሚፈለገው ለአልዩ አምባ ከተማ መሪ ማ/ቤት 3 ኪሜ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ከፈታ 200 ሰዓት የሚወስድ፡፡ ለስራው የሚሆን የማሽኑን ነዳጅና ሰርቪስ ተሽከርካሪ እንዲሁም ማንኛውም ወጪ ተጫራቹ እንዲችሉ እና በተጨማሪምእስራው ቦታ ድረስ ተጫራቾች ማሽኑን በራሳቸው ማጓጓ ማቅረብ ከሚችሉ ተጫራቾች ማሽኑን ተከራይቶ ከላይ የተጠቀሰውን መንገድ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው እና የሚያቀርቡት ማሽን የራሳቸው ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣በኪራይ የሚቀርብ ከሆነ ህጋዊ የማሽን የማከራየት ፍቃድ ካለው አካል ጋር በሕግ የተረጋገጠ ውል መቅረብ አለበት፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የቲን (TIN) ነበር ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረባ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከአንኮበር ወረዳ አልዩ አምባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 11 የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በመግዛት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የጠቅላላውን ዋጋ 1% የማያንስ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ስፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር ታሽጎ ማቅረብ ማስያዝ አለባቸው:: ሲፒኦ የሚያቀርቡ ከሆነ ለአንኮበር ወረዳ አአምባ ከተማ መሪ ማ/ቤት ተብሎ ካልመጣ ቢድ ቦንዱ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታው ሠነድ የሚገባው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የካላንደር ቀናት የሚወዳደሩ ዋጋ በጥንቃቄ በመሙላት ስርዝ ድልዝ ሣይኖረው የጨረታ ሰነዱን ኦርጀናል እና ፎቶ ኮፒ በመለየት በጥሩ ሁኔታ በማሽግ በኤንቨሎኘ ሙሉ አድራሻቸውን በመግለጽ ለአንኮበር ወረዳ አአምባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው የመጨረሻ ማስገቢያ ቀን በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ነው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በዚያው እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ታሽጎ ወዲያውኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሉ በተገኙበት ወይም ሳይገኙም ይከፈታል:: በ21ኛው ቀን የስራ ቀን ላይ ካሏለ በቀጣይ የስራ ቀናትና ተመሣሣይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙ የጨረታ ማስከበሪያው ያሲያዙት ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው አሽናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ቀሪ ዝርዝር ስራዎችን ከሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 21 18 51 50/ 09 21 14 07 64/ 09 15 24 86 75/ 09 47 37 08 14
ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአብክመ ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን ቢሮ
በሰ/ሸዋ ዞን መምሪያ በአንኮበር ወረዳ የአ/አምባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት