ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሰሜን ወሎ ዞን የዋድላ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለዋ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃ ፣
- ሎት 2 የጽ/መሣሪያ፣
- ሎት 3 የመኪና ጎማ፣
- ሎት 4 የጽዳት እቃ፣
- ሎት 5 የደንብ ልብስ፣
- በሎት 6 የመኪና እቃ በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ግዥለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች በስራ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- በሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ የሞሉትን ዋጋ ድምር 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከተጫራቾች አሸናፊው ውል የሚወስድበትን ዋጋ ድምር 10 በመቶ የውለታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና የስራ ማህተማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 50 ብር በመክፈል ዋድላ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው ቀን በተለያየ ፖስታ ዋናውንና ኮፒውን በማሸግ ከቀኑ 8፡30 ላይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን በማስገባት ይታሸጋል፡፡
- በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡00 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመወዳዳሪያ ፖስታው ይከፈትና በጨረታ ሂደቱ ለተላለፈው ውሣኔ ተገዥ የሆናሉ፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈትና በጨረታ ሂደቱ ለተላለፈው ውሣኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0334430121 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የዋድላ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት