የዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለወረዳው መሥሪያ ቤቶች
- ሎት 1. የጽህፈት መሣሪያዎችን፣
- ሎት 2. የፅዳት እቃዎችን፣
- ሎት 3. ፈርኒቸርና ኤሌክትሮኒክስ እና
- ሎት 4. የሠራተኞች ደንብ ልብስ
በግልጽ ጨረታ አወዳድረን መግዛት እንፈልጋለን።
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የሥራ ፍቃድ ያላቸው ሆነው፤
- ሀ. የዘመኑን ግብር በመክፈል የታደሰ ንግድ ፍቃድ መረጃ ማቅረብ የምትችሉ፣
- ለ. የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት መረጃ የሚያቀርብ፣
- ሐ. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆኑ የምስክር ወረቀት ከመወዳደሪያ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፣
- በ ጨረታው ለመወዳደር የጨረታ ማስረከቢያ በሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ – 3,000.00 ብር በደራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ ቤት ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 ተከታታይ ቀናት በሎት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር / በመክፈል የጨረታ መመሪያ ሰነዱን በመግዛት የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ ሰነድ የያዘ ፖስታ እስከ 22ኛው ቀን በማቅረብ ጨረታውን የያዘው ሳጥን በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ምናልባት 22ኛው ቀን የሥራ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ባይገኙም የጨረታሳጥኑን ከመከፈት አያግድም፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0111150061/199/መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
የደራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት