የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ወለጋ ዞን የጊምቢ ከተማ ገንዘብና ኢኮት/ጽ/ቤት በ2013 የበጀት ዓመት ለጊምቢ ከተማ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የጽሕፈት መሣሪያዎች
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፡
- የተለያዩ ፈርኒቸሮች
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣
- የስፖርት ቱታና ስኒከር ጫማ የተለያዩ የመኪናና የሞተር ሳይክል ጎማዎች
ተጫራቾች ማሟላት ያስባቸው
- በየዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2012 የመንግስት ግብርና ታክስ ከፍሎ የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ።
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ቫት ተመዝጋቢ ሆኖ ቲን (የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር) ማቅረብ አለበት።
- ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር ለጊምቢ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ገቢ አድርጎ ሰነዱን ከጊምቢ ከተማ ገ/ኢኮ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ወይም ግዥና ንብረት ዘርፍ አስተዳደር ክፍል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀን ውስጥ ጠዋት ከ2:30 – 6:30 ከሰዓት በኋላ ከ7:30 -11:30 በመግዛት ሞልተው ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ 2% (ሁለት ፐርሰንት) ጊምቢ ከተማ ውስጥ በሚገኘው በማንኛውም ባንክ ቅርንጫፍ በCPO አስገብቶ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የጨረታ አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ 10% (አስር ፐርሰንት) ህጋዊ ሰነድ (በባንክ የተረጋገጠ) ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
- ተወዳዳሪዎች ስርዝ ድልዝ የሌለውን የጨረታ ሰነድ ሞልቶ ዶክመንቱን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በተለያየ ካኪ ፖስታ ውስጥ አሽጎ ሀላፊነት ባለው ሰው በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና ማህተም ከተደረገ በኋላ ማቅረብ ይኖርበታል።
- አሸናፊው ያሸነፈበትን አቅርቦት በውሉ መሠረት በጊምቢ ከተማ ገ/ኢ/ትብብር/ጽ/ቤት በጊዜ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቶች ሰነዱ ከተከፈተ በኋላ የዋጋማሻሻያ ማድረግ አይችሉም።
- ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ዕቃ ለናሙና ማቅረብ የሚችል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ለማደናቀፍ ከሞከረ ከጨረታ ውጪ ሆኖ ለወደፊት በማንኛውም የመንግስት ግዥ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ይደረጋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) የስራ ቀን በጊምቢ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ከጠዋቱ 4:00 ላይ የጨረታው ሳጥን ተዘግተው በ4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል።
ማሳሰቢያ:- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር:-057-771-1783 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በምዕራብ ወለጋ ዞን የጊምቢ ከተማ ገንዘብና ኢኮ/ት/ጽ/ቤት