የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ወለጋ ዞን የጊምቢ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2013 የበጀት ዓመት ጊምቢ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት መምሪያ በከተማው ለሚሠሩ የጊምቢ ከተማ አስተዳደር የአሴት ማኔጅመንት ፕላን (ንብረት) ቆጠራ (Asset Management plan inventory Document) ከዚህ በታች እንደተገለፀው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- የ2012 ዓ.ም የመንግስት ግብር እና ታክስ የከፈለና የ2012 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያሳደሰ
- የአሴት ማናጅመንት ፕላን ንብረት ቆጠራ (Asset Management plan Inventory) ለማስራት በየዘርፉ ፍቃድ ያለው፡፡
- ማንኛውም ተወዳዳሪ የቫት ተመዝጋቢና ቲን መለያ ቁጥር ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችል
- የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ 200 (ሁለት መቶ) ብር ለጊምቢ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት መምርያ ገቢ አድርጎ ሰነዱን ከጊምቢ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት መውሰድ የሚችል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ አንድ ፐርሰንት (1%) ወይም (Cpo) በጊምቢ ከተማ የሚገኘው በማንኛውም ቅርንጫፍ ባንክ አስገብቶ መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የውል ማሰከበሪያ ጨረታ ያሸነፈበትን ዋጋ አስር ፐርሰንት (10%) ህጋዊ ሰነድ በባንክ የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ የሙያዊ ሰነድ ሞልቶ ወይም (technical document) በኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በተለያዩ ኤንቨሎፕ ወይንም በካኪ ፖስታ አሽጎ ሃላፊነት ባለው ሰው በያንዳንዱ ገፅ ላይ ፊርማና ሕጋዊ ማህተሞ አድርጎበት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱ ከተከፈተ በኋላ የሙያዊ ሰነድ ላይ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ለማደናቀፍ ከሞከረ ከጨረታ ውጭ በማድረግ ለወደፊትም በማንኛውም የመንግስት ግዥ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ከሆነ በዛው ቀን በጊምቢ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ከቀኑ በ6፡30 ሰዓት ታሽጎ ከሰዓት በኋላ የጨረታ ኮሚቴ በተገኙበት ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት የጨረታው ሰነድ ይከፈታል ፤16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የጨረታው ሰነድ የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡
- የሙያዊ ሰነድ ያሸነፉ ተጫራቾች በሌላ ደብዳቤ ለሁለተኛ ዙር ለፋይናንሻል ውድድር በድጋሚ በውስጥ መስታወቂያ ጥሪ እንደሚደረግለት ማወቅ ይኖርበታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ 0577710169/0577710769 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የምዕራብ ወለጋ ዞን የጊምቢ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት