የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች 1ኛ ዙር በ2013 የበጀት ዓመት ጨረታ አውጥቶ ከዚህ በታች ባለው ዝዝር ዕቃ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ፈርኒቸር፣
- የጽህፈት መሣሪያዎችና አላቂ ዕቃዎች፣
- የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሞተር ሳይክል፣
- የደንብ ልብስ፣
- ኤሌክትሮኒክስ፣
- የመኪና እና የሞተር ጎማ፣
- የቧንቧ ጥገና ዕቃዎች፣
- የመኪና እና የሞተር ጥገና፣
በግልጽ ጨረታ ህጋዊና አቅም ያላቸውን ድርጅቶችን አወዳድረው ለመጋዛት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ በመከተል ይህን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ቫት ከፋይ የሆኑ TIN Nummber ማቅረብ የሚችሉ
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎች ማሻሻል መቀየር እንዲሁም ሀሳቤን ቀይሬአለሁ ማለት አይችልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ ስመሳተፉ የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሚሠሩበት የንግድ ሥራ ዘርፍ ትክክለኛ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 በባንክ የተመሰከረለት CPO ማቅረብ አለበት ነገር ግን የማይክሮ ድርጅት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚመለከት የዋስትና ደብዳቤ በህጋዊነትካደራጃቸው አካል ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የዕቃውን ናሙና ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- አሸናፊ ከሆኑ ዕቃውን ጭነው እስከ መ/ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዕቃውን የተሰራበትን ሀገርና ሞዴሉን መግለጽ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጅናል በተለያዩ ፖስታ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ዋጋ የሚሞላው በተሸጠላቸው ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለባቸ፡፡
- ጽ/ቤታችን የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች 20% በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ስልክ ቁጥራቸውንና ፋክስ ቁጥራቸውን በትክክል ጽፈው መፈረምና ማህተም ማድረግ አለባቸው፡
- ተጫራቾች በመ/ቤቱ በወጣው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ መሰረት ትክክለኛ ዋጋ ላይ የዕቃዎችን መስፈርቶች አይነት መጠንና ብዛት በትክክል ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሰነዱ ሽያጭ የሚቆይበት ቀን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 13/12/2012 እስከ 3/13/2012 ዓ.ም የሥራ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ ጨረታውን የሚከፈተው በ4/13/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሉ በተገኘበት 4፡30 ሰዓት በይፋ በዛው ቀን ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ከምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ፅ/ቤት የማይመለስ ብር 200.00 ሻሸመኔ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ፅ/ቤት አዛ0ት 10000189138653 በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈው ነጋዴ ውሉን ስገባበት ቀን ውስጥ ዕቃውን አጠናቆ የማያስገባ ከሆነ በህግ እንደሚያስnይቀው ሃሙት አለበት፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ፡- ስል ቁጥር 0461104779 /046110,4279
በምዕራብ አርሲ ዞን የሻሽመኔ ወረዳ ገንዘብ
ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት