Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Others / Vehicle / Water Engineering Machinery and Equipment

በምስራቅ ሸዋ ዞን በሊበን ጭቋላ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2013 የበጀት ዓመት ለመንገድ መስሪያማሽኖችን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

በምስራቅ ሸዋ ዞን በሊበን ጭቋላ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2013 የበጀት ዓመት ለመንገድ መስሪያ ማሽኖችን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡

 1.  ዶዘር(CAT-D8R) ብዛት … 1
 2. ግሬደር (CAT-140HP) … ብዛት 1
 3. ሎደር (CAT or XCMG)… ብዛት –
 4. ሩሎ (16 tone). ብዛት-1
 5. የውሃ ቦቴ (Turbo or Starry Truck ) –ብዛት— 2
 6. ገልባጭ መኪናዎች ብዛት 10 ( 16-18 m3 )

ከተራቁጥር 1-6 የተጠቀሱትን ማሽኖች እና ገልባጮች በተጠቀሰው መስፈርትና ዓይነት ብቻ ሊያሟሉ የሚችሉተወዳዳሪዎችን ወይም ተጫራቾችን ማሳተፍ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተቀመጡትንመስፈርቶች አሟልተው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

 1. ማሽነሪዎችን ለማቅረብ አግባብነት (ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ(TIN No) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች እያንዳንዱን ማሽነሪ (ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትን) የሚያከራዩበትን ዋጋና ሞዴል እንዲሁምዓይነታቸውን እና ጉልበታቸውን በመግለጽ ከላይ የተጠቀሰውን ፍላጎት ማሟላት የሚችሉ ከሆነ ነዳጅና ቫትንጨምሮ በሰዓት ኪራይ ምን ያህል እንደሆነ ለጨረታው ታስቦ በተዘጋጀው ሰነድ ሞልተው በሰም በታሸገኢንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ በሊበን ጭቋላ ወረዳ ገንዘብናኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ገልባጮች ዋጋቸው በቢያጆ ሲሆን እሱም በኪሎሜትር ርቀት ልዩነት ነዳጅን ጨምሮ ተሞልቶ መቅረብ አለበት።
 4. ኣንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
 5. .ተጫራቾች በሚወዳደሩበትማሽን አይነት ከጠቅላላው ዋጋ1%CPOየጨረታ ማስከበሪያማስያዝ ይኖርባቸዋል።
 6. . ተጫራቾች ተወዳድረው ካሸነፉ ለኦፕሬተሮች እንዲሁም ለሾፌሮች የትራንስፖርት አገልግሎት ማቅረብይኖርባቸዋል፡፡
 7. አሸናፊው አካል ማሽኖችን ጭኖ ማስገባት እና ስራው ሲያልቅ ጭኖ የማስወጣት(ከሳይት ወደ ሳይት )ትራንስፖርት(ጉዞ) መቻል ይኖርበታል፡፡
 8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በሊበን ጭቋላ ገንዘብና ኢኮኖሚትብብር ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
 9. .የጨረታ ሰነዱ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ 30 ቀናት በኋላ ሆኖ ልክበዚሁ መጨረሻው እለት ልክ በ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋይከፈታል፡፡
 10.  ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 11. የማሽነሪዎችን ሊብሬ ማቅረብ የሚችል፡፡
 12. ተጫራቹ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 13. በጨረታው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 14. ማንኛውም ተጫራች ከጨረታ ማስገቢያ ሰዓት ውጭ ከመጣ ተቀባይነት የለውም፡፡

ማሳሰቢያ፡- የተባለው 30ቀን ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ጨረታው የሚከፈተው የሥራ ቀን ብቻ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0228126753/0910744234/0912650236

በምስራቅ ሸዋ ዞን ሊበን   ጭቋላ ወረዳ ገንዘብናኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት