የጨረታ ማስታወቂያ
በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የጃርሶ ወረዳ ፍ/ቤት በ 2013 ዓ.ም ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤
ስለሆነም ተወዳዳሪው ድርጅት ማሟላት ያለበት፤
- የንግድ ፈቃድ ያለው የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- ዕቃዉን በተፈለገው ጥራት፣ ብዛትና ደረጃ ማቅረብ የሚችል።
- መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ ማምጣት የሚችል፡፡
- የእያንዳንዱን ዋጋ በመሙላት ማቅረብ የሚችል።
- የዕቃውን ዝርዝር ሰነድ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመክፈል መግዛት የሚችል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000,00 (አስር ሺ ብር) ማስያዝ የሚችል።
- ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በፖስታ በማሸግ በሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- የጨረታውን ሳጥን ልክ በአስራ ስድስተኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ተወካይ ባለበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ እንዳሸነፈ ወዲያውኑ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 ( አሥር ሺ ብር) የጨረታዉ ተሽናፊ ለሆኑት ወዲያውኑ ይመለሳል።
- የተሻለ ሁኔታ ካገኘ መስሪያ ቤቱ በጨረታዉ አይገደድም።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት
የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የጃርሶ ወረዳ ፍርድ ቤት