ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጭልጋ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ክፍያና ንብረት አስ/ደ/የስራ ሂደት በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ የተለያዩ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 3. ሌሎች አላቂ መሣሪያዎች ፣
- ሎት 4. የህትመት አቃዎች፣
- ሎት 5. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ሎት 6. የደንብ ልብሶች ናቸው፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው
- የግዥው መጠን 200000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ አገልግሎቶችን አይነትና መገለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ማስረጃ ቢያስፈልጋቸው ከስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 5 ስልክ ቁጥር 09 88 53 08 64
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዱን ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ለሎት 1 ብር 1000፣ ለሎት 2. 100 ብር፣ ለሎት 3. 100 ብር ፣ ለሎት 4. 600 ብር ፣ ለሎት 5. 1000 ፣ ለሎት 6. 500 ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫንች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የጭልጋ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በጎንደር ከተማ ከፍ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/ አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 7/03/2013 ዓ.ም 21/03/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 15 ከላይ ከተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ሲሆን ይኸውም ከ 07/03/2013 እስከ 21/03/2013 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከላዊ ጎን/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት የክፍያና ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ቀን 22/03/2013 ዓም ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኝ ዕቃዎችን በመቶ የመጨመር /የመቀነስ/ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ማዕከላዊ ጎን/ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ነው፡፡
- ማሳሰቢያ፡- ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት በጭ/ወ/ፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል መውሰድ አለበት፡፡
የጭልጋ ወረዳ ፍ/ቤት