የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/16-09B/GoFA 1/ 0045/2020
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የጎፋ 1 አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት (1609B) የሳኒተሪ እቃዎች አቅርቦትና ገጠማ (Domestic Water Supply Booster Pump supply & Fix) በዘርፉ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መሰረት አስፈላጊውን ግብዓት በማቅረብ መስራት የሚችሉ ተጫራቾን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ተጫራቾች፡
- የ2012 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
- VAT የተመዘገበችሁበትን ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No) ማቅረብ የምትችሉ
- በመንግስት ግር አቅርቦት ኤጀንሲ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከመንግስት የግብር ዕዳ ነፃ መሆናቸው (Tax Clearance) ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅታችን የግዥ መመሪያ መሰረት በፕሮጀክታችን ትክክለኛ ስም MEKEL CON ENI YEGOFA YEM BEI AP PH በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ ብቻ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዕለቱ ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የተጫራቾች ስነድ ቴክኒካል እና ፋይናሻል ተለያይቶ መቅረብ ይኖርበታል።
- የተጫራቾች ቴክኒካል ዶክመንት ተገምግሞ መስፈርቱን ያሟላ ተጫራች ብቻ ፋይናሻል ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ድርጅቱ ጨረታው ከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ
ጎፋ-1 አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት (16-09B)
(ጎፋ ካምፕ ግቢ ውስጥ)
+251118886649 /+251 11888 6631