በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የአርሚ ፋውንዴሽን አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት /16-01B/ ምዕራፍ ሁለት በሰሚት አካባቢ ለሚሰራቸው የህንፃ ግንባታ የውሃ ስርገት መከላከያ ስራ (Cementious Water Proofing Work) በሚቀርበው ዝርዝር መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የአርሚ ፋውንዴሽን አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት /16-01B/ ምዕራፍ ሁለት በሰሚት አካባቢ ለሚሰራቸው የህንፃ ግንባታ የውሃ ስርገት መከላከያ ስራ (Cementious Water Proofing Work) በሚቀርበው ዝርዝር መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ብቻ ከፍለው ከፕሮጀክቱ ፋይናንስ ክፍል በመውሰድ በተያያዘው የስራ ዝርዝር መሰረት የሚሰሩበትን ዋጋ በመሙላት በፖስታ አሽገው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በፕሮጀክቱ ግቢ የግብአት አቅርቦት እና አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በእሮብ7/07/2012ዓ/ም ከረፋዱ 4.00 ሰዓት ይዘጋል፡፡ በዕለቱ 4.30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤፤

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈረት፡-

1)    ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና TIN No ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2)    ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸውን የሚገልፅ ታክስ ክሊራንስ (tax clearance) ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡

3)    ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡

4)    ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማ እና ሙሉ ስም እንዲሁም አድራሻቸውን በመግለፅ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5)    ተጫራቾች  በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው ሆነው የሚስሩባቸውን የእጅ መገልገያ እና ሎሎች የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች ማቅረብ አለባቸው፡፡

6)    ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዱ ለየብቻ ታሽጐ መቅረብ ያለበት ሲሆን የቴክኒካል ሰነድ በእለቱ የሚከፈት ሲሆን ፋይናንሻል ሰነድ የሚከፈቻ ቀን ወደ ፊት ይገለፃል፡፡

7)    የስራው መጠን ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡

8)    ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ሰሚት ኮንዶሚኒየም 2ኛ በር ከጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ወረድ ብሎ

ስ/ቁ 011-8-34-92-41

ከሠላምታ ጋር

ፕሮጀክቱ