በድጋሚ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር/DCE/17-05B/GOFA 2/0034/2019
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የአርሚ ፋውንዴሽን አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት /16-01B/ ምዕራፍ ሁለት በሰሚት አካባቢ ለሚሰራቸው የህንፃ ግንባታ አገልግሎት የሚውል አጣና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ፕሮጀክቱ ድረስ ከሚያቀርቡ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።
1.የአጣና ግዥ
ስለሆነም ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ብቻ ከፍለው ከፕሮጀክቱ ፋይናንስ ክፍል በመውሰድ በተያያዘው ዝርዝር መሰረት የሚያቀርቡበትን ዋጋ በመሙላት በፖስታ አሽገው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 /አምስት/ የስራ ቀናት በፕሮጀክቱ ግቢ የግብአት አቅርቦት እና አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው: ጨረታው በ01/10/2012ዓ/ም ከረፋዱ 4.00 ሰዓት ይዘጋል። የፋይናንሻል በዕለቱ 4.30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል::
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈረት፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና TIN No ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸውን የሚገልፅ ታክስ ክሊራንስ (tax clearance) ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማ እና ሙሉ ስም እንዲሁም አድራሻቸውን በመግለፅ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበቸው
- የስራው መጠን ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
- ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ሲገኙ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና( Unconditional Bank Guarantee ማስያዝ አለባቸው
- ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ
ሰሚት ኮንዶሚኒየም 2ኛ በር ከጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ወረድ ብሎ
+0118-34-92-41