የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክ/ከ/አስተዳደር በዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የመንግስት ግዢ አስተዳደር ቡድን የግልጽ ጨረታ ቁጥር 02/2012 ዓ.ም በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግስት ግዢ አስተዳደር ቡድን ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ መሸጥ ይፈልጋል።
- ሎት 1. የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎችን መግዛት፡- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር ብቻ
- ሎት 2. የሚወገዱ ንብረቶች፡- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000.00 /ሦስት ሺ ብር ብቻ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግስት ግዢ አስተዳደር ቡድን በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
2. ተጫራቾች፡
- ሀ. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው እና በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ /በሚመለከተው አካል/ በአቅራቢነት የተመዘገበ፣
- .ሊ. በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ እና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችል።
- በየሎቱ በተቀመጠው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን CPO የልደታ ክ/ከ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የመንግስት ግዢ አስተዳደር ቡድን በሚል ስም በማሰራት ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግሥት ግዢ አስተዳደር ቡድን የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 25% ጨምሮ ወይም የመግዛት መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ ትራንስፖርት በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግስት ግዢ አስተዳደር ቡድን ዕቃ ግምጃ ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ10ኛው የሥራ ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው ሳጥን በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግሥት ግዢ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።የጨረታው ቀን መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው:: ናሙና ለማይቀርብባቸው የዕቃ ዓይነቶች ከመስሪያ ቤታችን በቀረበው ስፔስፊኬሽን መስፈርት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ልደታ ፍርድ ቤት አካባቢ ከንግድ ባንኩ ጀርባ።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 01 18 54-71-87
በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን