ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
- ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች
- አገልግሎት የሰጡ የመኪና መለዋወጫዎች
- ያገለገሉ ጎማዎች
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50.00/ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ የሰነዱ መሽጫ ቦታ ጎማ ቁጠባ ፖሊስ መምሪያ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 102 ነው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶችን ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በክፍለ ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ 6ተኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዋጋ የሞሉትን ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛዉ ቀን በ 8:00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከቀኑ 8:30 ላይ በክፍለ ከተማው በፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ጠቅላላ አገልግሎት 6ተኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች የገንዘብ መጠኑን በቁጥርና በአሃዝ መፃፍ ይጠበቅባቸዋል
- የዘገየ ጨረታ በጨረታ መክፈቻ ላይ ተቀባይነት የለውም
- ከፍተኛው ጨረታ በመነሻነት በተያዘው ዋጋ ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ ኮሚቴው ከፍተኛውን የጨረታ ዋጋ ሊቀበል ይችላል፡፡
- ጨረታ የወጣውን እቃዎች ሰነድ መግዛቱ ከተረጋገጠ በኋላ ደረሰኙን በማሳየት የንብረቱ ዝርዝር የሚገኝበት ቦታ በልደታ ክ/ከተማ ጎማ ቁጠባ ፖሊስ መምሪያ ቅጥር ግቢ እና ዛገዌ ህንጻ ጎን በሚገኘው 6ኛ ፎቅ በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላል
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ከ/ክፍለ ከተማው ግቢ በ 2 ቀን ውስጥ ማንሳት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በተጠቀሰው ቀን ማንሳት ካልተቻለ ባደረበት ቀንብር 500 እየጨመረ የሚሄድና ከ5 ቀን በኋላ ንብረቱ ይወረሳል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያና ጥያቄ
በልደታ ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት መጠየቅ ይችላሉ የመስሪያ ቤቱ ስልክ ቁጥር 0118548855
የልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው
ሀብት ልማት ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር
ጠቅላላ አገልግሎት ደጋፊ የስራ ሂደት