ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር 01/2013
በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን
- ሎት 1 የተለያዩ ህትመቶች የጨረታ ማስከበርያ በብር 500.00
- ሎት 2. የኤሌክትሪክ ገመድ የጨረታ ማስከበርያ በብር 500.00
- ሎት 3, የተለያዩ ደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበርያ 500.00
- ሎት 4 የተለያዩ የደንብ ልብስ ስፌት የጨረታ ማስከበርያ 500.00
- ሎት 5. ቋሚ እቃ የጨረታ ማስከበርያ 500.00
- ሎት 6. የጽህፈት መሳሪያ የጨረታ ማስከበርያ 500.00
- ሎት 7. የፅዳት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበርያ 500.00
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ/አገልግሎት መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገበ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ የተረጋጠ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህ/ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በወ/ሮ በለጥሻቸው ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥ 5 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ውጭና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ
የመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር ፡ 0902395757 / 0912350364
በልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጣቢያ
ወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ