የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 አስተዳድር ጽ/ቤት በስሩ ላሉ ጽ/ቤቶች በ2013 ዓም በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስን የኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር እቃዎች አወዳድሮ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. የጽሕፈት መሳሪያዎች
- ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 3 የደንብ ልብስ
- ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 5 ፈርኒቸር እቃዎች
- ምድብ፡- የጽሕፈት መሳሪያ __2000 ብር
- ምድብ፡- የጽዳት እቃዎች ___2000 ብር
- ምድብ፡- የደንብ ልብስ…………………2000 ብር
- ምድብ፡- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች –2000 ብር
- ምድብ : ፈርኒቸር ዕቃዎች 2000 ብር
ስሆነም:
- በጨረታው መወዳደር የሚችሉትን የንግድ ፍቃድ ያላባቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ያላቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% (ሁለትፐርሰንት) በባንክ የተመሰከረ ቼክ (CPO) ከጨረታው ፖስታ ጋር ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ተከታታይ ቀናት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ መሃንዲስ ኮንዶምንየም አጠገብ ሶልያና ህንጻ ፊት ለፊት/ የወረዳ 8 አስተዳደር ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁር 103 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳሩበትን ዋጋ ማስታወቂያ ከወጣበት 10ኛ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በወረዳ 8 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት 1ኛፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታ ከወጣበት እለት አንስቶ በአስረኛው ቀን በ 8:00 ሠዓት፡፡ነገር ግን oኛው ቀን ስራ ቀን ካልዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት በተወዳደሩባቸው ከምድብ 1 እስከ ምድብ 4 ዝርዝር እቃዎች መሰረት የእቃውን ናሙና አስቀድሞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ ያለውን ዋጋና ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው
- ተጫራቾች በቀረበው የፍላጎት በመጠየቂያውም ሆነ ጨረታው ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ማኖር የለባቸውም፡፡
- ተጫራቶች ጨረታውን ካሸነፉ የጨረታ ማስተካከያ መጠየቅ አይችሉም።
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሽነፉ የጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ዋጋ 10 ፐርሰንት በቼክ ወይም በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባችው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና የዕቃ ዋጋ በመጠያቂያው ላይ ከሞሉ በኋላ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒውን በታሸገ ፖስታ ማስገባት አለባቸው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት በተወዳደሩበት ዝርዝር እቃዎች መሰረት ናሙናውን አስቀድሞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ቫት ተጨምሮ ያለውን ዋጋ እና ከቫት ውጪ የለውን ዋጋ መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚያቀርቡት የእቃ ዋጋው ላይ ቫትን መጨርና አለመጨመሩን በግልጽ በጽሑፍ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የእቃን በግለጫ (ዓይነት) በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
አድራሻ፡- በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ከባልቻ ሆስፒታል ጀርባ ከፍ ብሎ መሃንዲስ ኮንዶሚንየም አጠገብ (ሶልያና ህንጻ ፊት ለፊት) ወረዳ 8 አስተዳደር ሕንጻ 1ኛ ፎቅ
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 አስተዳድር ጽ/ቤት