ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር -LS/C
F/E/D 02/2013
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4/ፋ/ጽ/ቤት አስተዳደር ጽህፈት ቤት ስር ላሉት ጽህፈት ቤቶች በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች የግዥ መለያ ቁጥር L/S/C F/E/D/ 02/2013
- ሎት1 የቋሚ ዕቃዎች የኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000
- ሎት 2 የደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1,000
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር – 100 በመክፈል በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር -103 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በወረዳው ቢሮ ቁጥር -103- ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተሽጎ በእለቱ 8፡30 ሰዓት በወረዳው ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፡፡ የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት -1 ሎት-2– ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን– በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጅትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስራቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- በተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ ለጨረታው ከቀረቡ የዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ መ/ቤቱ እስከ 20 በመቶ ለመጨመር ወይም ለመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር፡-0118 72 22 82/0112 30 00 02
አድራሻ፡– ልደታ ክ/ከተማ አብነት ልዩ ቦታ ጆስ ሃንሰን አካባቢ ኣዲሱ ሱማሌ ተራ ገባ ብሎ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ቢሮ ቁጥር 103
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4
አስተዳደር ፋይናንስ ጽህፈት ቤት