ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2013
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ መስከረም አንድ አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚያስፈልጉ
- ሎት 1. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00
- ሎት 2 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር3000.00
- ሎት 3. የደንብ ልብስና ጫማ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000.00
- ሎት 4.ቋሚ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6000.00
- ሎት 5. የአይቲ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00ብቃት ያላቸውን በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤በመንግስት ግ/ን/አ/ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፤ የቲን ነምበር ያላቸው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) በመክፈል መስከረም አንድ አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት አንስቶ ለተከታታይ 10የስራ ቀናት መስከረም አንድ አጸደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባትይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትበአስረኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከቀኑ 4:30 በት/ቤቱ ቤተ-መፅሀፍት ይከፈታል፡፡የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜናእሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀንበተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ውጪና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ት/ቤቱ እስከ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነበከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ ማብራሪያ መስከረም አንድ አፀደ ህፃናትና መ/ደ/ት/ቤት ስልክ ቁጥር፡-0115157392
- አድራሻ:-ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ፊት ገባ ብሎወረዳ 1ጽ/ቤት አጠገብ
በልደታ ክፍስ ከተማ ወረዳ አንድመስከረም አንድ አፀደ ህፃናትና
የመ/ደ/ት/ቤት