ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክፍለ ከተማ ህዳሴ ፍሬ ጤና ጣቢያ በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡
- ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 3 የህክምና መሳሪያ
- ሎት 4 ቋሚ ዕቃዎች
- ሎት5 የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 6 የደንብ ልብስ
- ሎት 7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
- ሎት 8 መድሃኒቶች
- ሎት 9 ህትመት
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ ሎቶችን ብቃት ያላቸው እና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ መ/ቤቱ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑ ግብር የከፈሉ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ–ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ በሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች 10% (አስር ፐርሰት) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር በተለየ ፖስታ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 በመከፈል ሰነዱን መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን 1 ኦርጅናል እና 1 ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናቶች ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰአት ተዘግቶ በዛው እለት ከጠዋቱ 3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ። የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ የስራ ሰዓት ይከፈታል።
- የጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሚያመርቱባቸው ዕቃዎች ላይ ብቻ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ከተደራጁበት ተቋም በዘርፋቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር በመደመር ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- በጨረታ መከፈቻ ላይ የዘገየ ተጫራች በውድድሩ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዢ ፈጻሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– ከከፍተኛ ፍ/ቤት ወደ ሳርቤት በሚወስደው አስፋልት ልደታ
ክፍለ ከተማ ወረዳ ላይ ቢሪሞ ሜዳ ገባ ብሎ ወጣት ማዕከል
ስልክ ቁጥር 0118593064
በልደታ ክፍለ ከተማ የህዳሴ
ፍሪ ጤና ጣቢያ