ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉዱሩ ወረዳ ፍ/ቤት ውስጥ ለሚገኙ መ/ቤቶች የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ
- የጽሕፈት መሣርያዎች፣
- የደንብ ልብስ ፤
- ስልጠና መሣሪያዎች፤ የአላቂና የጽሕፈት መሣሪያዎች፣
- የመኪናና፤ የሞተር ሳይክል፤ ጎማዎች፣ ከለማነዳሪዎች፣
- የግንባታ ዕቃዎችን፤ የቋሚ ዕቃዎች እና፤
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት፤የሚገባቸው መስፈርቶች፡
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው/ያላት፡፡
- የ2012 ወይም 2013 ዓ.ም.ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና ማሰረጃ ያላቸው፡፡
- የአሸነፈበትን ዕቃ እስከ ገዱሩ ወረዳ ፍ/ቤት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ የሚችል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና( Bid Bond) የሚመለስ ገንዘብ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ (CPO) 10,000.00 (አሥር ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማሰያዝ ይኖርበቻዋል::
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15ኛ ቀን ተከታታይ ሥራ ቀናት ዘወትር፤ በሥራ ሰዓት፤ ከላይ በተጠቀሰው በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉዱሩ ወረዳ ፍ/ቤት በመቅረብ ዋጋ ማቅረቢያዎችን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል::
- የጨረታ ሰነዱን ተጫራቾች የጉዱሩ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ቀርበው ለእያንዳንዳቸው ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) ከፍለው መግዛት ይችላሉ::
- ጥቃቅንና አነስተኛ ማይክሮ ኢንተርፕራይዞች ከተደራጁበት መ/ቤታችው ለዋስትና ደብዳቤ ከሰነዶቻቸውና ገንዘብ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ (CPO) 10,000.00 ( አሥር ሺህ ብር) ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታ ሳጥን በ15ኛው ሥራ ቀን ከቀኑ 11:30 ሰዓት ላይ ይዘጋል::
- የጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝና የሚገዛቸውን ዕቃዎች በ20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 057 6630108 ደውሎ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
የጉዱሩ ወረዳ ፍርድ ቤት