ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2013
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሻምቡ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዘመን በስሩ ለሚገኙ መ/ቤቶች የሚያገለግሉ
- የቢሮ ውስጥ ዕቃዎችን፣
- የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣
- የጽዳት ዕቃዎችን፣
- አላቂ ተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችንና የሰራተኛ ደንብ ልብሶችን፣
- የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን፣
- ፈርኒቸሮችን እና ሌሎችንም ለቴከኒክና ሙያ ሥልጠና ት/ቤት የሚያገለግሉ የተለያዩ ለማስተማሪያ አገልግሎት የሚውሉ ማቴሪያሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁም ዘመሠረት ተጫራቶች በጨረታው ለመካፈል የሚከተሉትን መስፈርቶች መከተል ይኖርባቸዋል፡፡
- ሕጋዊ የሆነ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የ 2013 ፍቃድ ያሳደሱ።
- የ2013 ፍቃድ ያላሳደሱ ከሆነ ከገቢዎች ጽ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገቡና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ማስረጃ የሚያቀርቡ።
- በእቅራቢዎች ዝጉስ መመዝገባቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ።
- ለሚሸጡት ዕቃ በሕጋዊ መንገድ ደረሰኝ በሚመለከተው አካል እሳትመው ያላቸው።
- መ/ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ በሚገዛቸው ዕቃዎች ላይ እስከ 20% መጨመር ወይንም መቀነስ የሚችል መሆኑን ተቀብለው የሚወዳደሩ።
- ተጫራቶች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች እስከ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡
- ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎችን ለማቅረብ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (cpo)ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ሕጋዊ በሆነ ባንክ ብር 5000.00(አምስት ሺ ብር) ማስያዝ ወይንም በእጅ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዶቻቸውን ኦርጅናሉንና ኮፒውን አንዳንድ በተለያየ ፖስታ አሽገው ስማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
- ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ 15ተኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተወዳዳሪዎች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተወዳዳሪ የጨረታ ሠነዱን በማይመለስ ብር 150.00(በአንድ መቶ ሃምሳ ብር) ከሻምቡ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ነጋዴ ሳለው ንግድ ዘርፍ ተወዳድሮ የሚሸጥበትን ዋጋ ከቫት ጋር በፖስታ አሽጎ በመ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በማቅረብ መወዳደር ይችላል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መሠረዝ ይችላል፡፡
- ተጨማሪ መረጃ፡ በስልክ ቁጥሮች / 0913-96-2576 /09 2577-2512 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሻምቡ ከተማ
ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት