የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የምስራቅ ዕዝ ግ/ወ/ቁጥር 04/2013 ዓ.ም
በሀገር መከላከያ ሚ/ር የምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ በ2013 በጀት ዓመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውሉ፡
- የግንባታ ዕቃዎች
በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በዚሁ መሠረት በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ንግድ ፈቃድ የዘመኑ ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት ያላቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀትና የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ ከ2:30 እስከ 600 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ7:30 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሐረር ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ በሚገኘው ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ እስከ ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ/ም የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ::
ጨረታው ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐረር ቤተ መንግስት መዝናኛ ክበብ ይከፈታል ፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 025 666 85 25/ 025 666 02 00 የውስጥ መስመር 289/292
በሀገር መከላከያ ሚ/ር
የምስራቅ ዕዝ ማ/መምሪያ ግዥ ቡድን
ሐረር