የጨረታ ማስታወቂያ
በሀገር መከላከያ ሚ/ር የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ግዥ ባለው በጀት፡-
- በሎት 1:- Antiseptics & Disinfectants, Radiology & Imaging Materials
- በሎት 2:- Different Reagents, Laboratory& Pathology Materials እና
- በሎት3:-Dental Materials ግዢዎች የግዢ መለያ ቁጥር መከ/ጤ/ዋ/መም/ግ/ጨ-06/2013 ግዥዎችን በአገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ (Tax Clearance Certificate) ፣ ተጫራቹ በገንዘብ ሚ/ር የነጋዴ ድርጅቶች መዝገብ የተመዘገበ መሆኑን እና ከኢትዮጵያ የምግብ፣መድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የተሰጠ የታደሰ ሰርትፍኬት፣ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከናወነው በግልጽ ጨረታ ሥነ ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ባወጣው የመንግሥት የግዥ አዋጅ መሠረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው::
- ፍላጎት ያላቸው ብቁ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ሊያገኙ የሚችሉት መከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ግዥ ቡድን ሲሆን፤የጨረታ ሰነዶች የሚመረመሩበት ከዚህ በታች በቁጥር 7 (ሀ) በተገለጸው አድራሻ ነው፡፡
- ከላይ ለተጠቀሰው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ከዚህ በታች በቁጥር 7 (ሀ) በተገለጸው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታው ሰነድ የሚላከው በማንኛውም መንገድ ሲሆን፤ ሰነዱ ቢጠፋ ወይም ቢዘገይ ኃላፊነት የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች በቁጥር 7«ሐ» በተገለጸው አድራሻ እስከ ህዳር 29 ቀን 2013 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ብር ለጨረታ ለሎት፡-1 ብር 60,000.00፣ ለሎት፡-2 ብር 350,000.00 እና ለሎት፡-3 ብር 40,000.00 ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም የተጫራች ወኪሎች በተገኙበት በቁጥር 7 «መ» በተገለጸው አድራሻ ህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መከላከያ ጤ/ዋ መምሪያ ግዥ ቡድን እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለማብራሪያና ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ፡-
- ሀ. ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ መከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ግዥ ቡድን ጦር ኃይሎች ቅጥር ግቢ
- ስልክ ቁጥር፡– 251-113-729-325
- ለ. ሰነዱ ወጪየሚሆንበት አድራሻ
- ሒ. ጨረታው የሚላክበት አድራሻ መከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ግዥ ቡድን ጦር ኃይሎች ቅጥር ግቢ
- ስልክ ቁጥር፡– 251-113-729-325
- 7(ሀ) ይመልከቱ
- መ. ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ
- 7(ሓ) ይመልከቱ
በአገር መከላከያ ሚኒስቴር
መከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ግዥ ቡድን