የጨረታ ማስታወቂያ
የማስታወቂያ ቁጥር ደ/ዕዝ ግ/ቡ A-5/2012
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የመኖሪያ ቤት በግልፅ አወዳድሮ ለማሳደስ ይፈልጋል፡፡
- የመኖሪያ ቤት ዕድሳት አገልግሎት ግዥ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በጨረታው ሊወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የጨረታ አይነቶች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ እና Gc-6እና ከዚያ በላይ የሆነ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ / ከፋይነት | ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መመሪያ መሰረት በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- .ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው
- የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ ጋር የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል – ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታውጆ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ቀናት ውስጥ ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው የደ/ዕዝ ጠ/ መምሪያ ስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ግንቦት 5 /2012 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡ 00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡ 30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደ/ዝ ጠ/መምሪያ ስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈፅሙ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPo ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-328 0020 ይደውሉ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር
የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ /ቶጋ/