Architectural and Construction Design / Building Construction / Contract Administration and Supervision / Engineering

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ቢሾፍቱ በሚገኘው ይዞታው ውስጥ አጥር፣ የአቬሽን ክሊኒክ እና የተማሪዎች ዶርሚተሪ እድሳት ስለሚያስገነባ አማካሪ ድርጅት (Consultancy) የአገልግሎት ግዥ በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ግልፅ ጨረታ 07/2012

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ቢሾፍቱ በሚገኘው ይዞታው ውስጥ አጥር፣ የአቬሽን ክሊኒክ እና የተማሪዎች ዶርሚተሪ እድሳት ስለሚያስገነባ አማካሪ ድርጅት (Consultancy) የአገልግሎት ግዥ በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (Value added tax) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣

4. በኮንስትራክሽን አማካሪነት ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ሰርተፍኬት/ያላቸው፣

5. በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጨረታ ላይ እንዳይሣተፉ ያልታገዱ እና በመንግስት የአገልግሎት ግዥ የግልፅ ጨረታ አፈፃፀም መመሪያ መስፈርት መሰረት ለመወዳደር ብቁ የሆኑ፣

 • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ሲሞሉ ከተ.. በፊት ያለ የነጠላ ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፣
 • ጨረታው መሣተፍ የሚችሉደረጃ አንድ አማካሪ ድርጅቶች ብቻ ይሆናሉ፣
 • ለአምስት አመት ተከታታይ የሠሩትን የኦዲት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ፣ በየትኛውም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተመሳሳይ ኘሮጀክቶች ህጋዊ ውል ገብተው በውላቸው መሠረት ያለምንም ጉድለት አጠናቀው ማስረከባቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፣
 • አማካሪ ድርጅቶች ለውድድር ያቀረቡትን የቴክኒክ ብቃት መወዳደሪያ ሰነዶች ዋጋ ኦርጅናል/ኮፒ ሲጠየቁ ማመሳከር አለባቸው ይህ ተጣርቶ ኮፒ ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ተመሳሳይ ካልሆነ ተጫራቹ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፣
 • ቴክኒካል ውድድሩን ያላለፈ ተጫራች ፋይናንሻሉ አይከፈትም፣

የጨረታ ማስከበሪያ (unconditional Bank Guarantee) የክፍያ ማዘዣ CPO የገንዘብ መጠን 100,000.00 ብር ይሆናል፣

 • የጨረታ ሰነድ ተጫራቾች በመመሪያ መሠረት ተሞልቶ ቢድ ቦንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እና በሁሉም ዶክሜንት ላይ ህጋዊ የድርጅቱ ባለቤት ፊርማና ማህተም መደረግ ይኖርበታል፣
 • ተጫራቾች የማጭበርበር፣ ሙስና እና ማታለልን በተመለከተ ላለመፈፀም በኢትዮጵያ ህጐች የተደነገገውን የሚያስከብርና የሚያከብር ግዴታ አለበት፣
 • የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ፣ (አሸናፊ የሆነ ተጫራች ማሸነፋ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 07 ቀናት በኋላ ለውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ካሸነፉበት ዋጋ 10% (Conditional Bank Guarantee) አስይዞ ውል መዋዋል ይኖርበታል፣
 • ማንኛውም ተጫራች አማካሪ ድርጅት ዋጋ ሲሞሉ በጨረታ ሰነዱ በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
 • ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ማድረግ፣ ከጨረታው ራሣቸውን ማግለል፣ ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት አይችሉም፣
 •  ማንኛውም ተጫራች አማካሪ ድርጅት በሚያቀርበው ማስረጃ (ዋጋ ላይ) ስርዝ ድልዝ (ፍሉድ) ካለበት ከጨረታ ውጭ ይሆናል፣
 • ለጨረታው የተሰጠው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 90 ቀናት የማይቀር (የፀና) ይሆናል፣

ጨረታ የሚከፈትበትና የሚዘጋበት ቀን፡

 • ይህ ጨረታ ከወጣበት ሰኔ 1 ቀን 2012 / እስከ ሰኔ 15 ቀን 2012 . ተከታታይ ባሉት 15 የስራና የበዓል ቀናቶችን ጨምሮ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል የተከፈለበትን ህጋዊ ደረሰኝ በማሳየት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በሶፍት ኮፒ ደብረ ዘይት በሚገኘው አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በዋናው በር በመምጣት መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፣ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 15 ቀን 2012 . ከቀኑ 800 ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 830 ሰዓት ላይ ደብረዘይት ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የአየር ኃይል መኰንኖች ክበብ ውስጥ ይከፈታል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 011 4 33 84 03 ወይም 011 4 33 80 40 የውስጥ መስመር 1330/1446 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ