የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር : ሰላም ማስከበር
ማዕከል DPKC/OT/02/2013A
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ/ቁ |
የጨረታው ዓይነት |
የመዝጊያና የመክፈቻ ቀን |
ሎት -1 |
የሲቪል አልባሳት እና የስፖርት ትጥቆች |
ማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም.ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 4:30 ይከፈታል፡፡ |
ሎት -2 |
የአላቂ የፅህፈትና የፅዳት ዕቃዎች |
ማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም.ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ |
ሎት -3 |
የተለያዩ ኤሌከትሮኒክስና የፈርኒቸር ዕቃዎች |
ረቡዕ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ |
ሎት -4 |
የተለያዩ የግንባታ፣ የቧንቧና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች |
ረቡዕ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ |
ሎት -5 |
የሆቴል ኪራይ አገልግሎት
|
ሐሙስ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ |
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ለተጨማሪ ዕሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣ የአቅራቢነት የድህረ–ገፅ ምዝገባ የምስክር ወቀረት፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት እና የቲን ሰርተፍኬት ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነ ስርዓት እና ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ባወጣው የመንግስት የግዥ አዋጅ መሰረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው፡፡
- ከላይ በመግለጫ ለተጠቀሱት የጨረታ ሰነዶች ለእያንዳንዳቸው ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዶችን ከዘህ በታቶ በቀራ ቁጥር 7 በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታው ሰነድ የሚቀርበው በአካል ቢሮ ድረስ በመምጣት ሲሆን ከዚህ በላይ በዝርዝር ከተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ውጭ ዘግይቶ ለሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ኃላፊነት የማንወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራች በሀርድ ኮፒ በመጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ያልተካተቱ የተለያዩ የጨረታ መመሪዎች ስላሉ ማንኛውም ተጫራች በሶፍት ኮፒ ለመውሰድ ባዶ ሲዲ ብቻ ይዞ መምጣት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ናምና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎቶ ከጨረታ መክፈቻ አንድ ቀን ቀድሞ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከተጠቀሰው ቀን በኃላ የሚመጣ ናሙና ተቀባይነት አይኖረውም።
- መስሪያ ቤታችን እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ እና የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ የሚያገለግል
አድራሻ :- ከሚኒሊክ ሆስፒታል ወደ ጃንሜዳ በሚወስደው መንገድ መከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል
ስልክ ቁጥር 01-11-54-01-50
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰላም
ማስከበር ማዕከል ግዥ ቡድን