የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር የልዩ/ዘ/ኃ ግ.ጨ 001/2013A
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የትራንስፖርት አገልግሎቶች ማለትም፡
- 12 ሰው የሚጭን 01(አንድ) ሚኒባስ
- 30 ሰው የሚጭን ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ ሁለት መለስተኛ አውቶብስ 01(አንድ)
- 60 ሰው የሚጭን ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ ሁለት 01(አንድ) አውቶብስ በጨረታአወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች:
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት አገልግሎት ጋር በቀጥታ ግንኙነት (ተዛማጅነት) ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ያላቸው፡፡ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ የመኪናዎቹን የመድን ዋስትና እና የመኪናዎቹን የባለቤትነት (ሊብሬ) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በልዩ ዘመቻዎች ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ስም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን ብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን ውስጥ ባሉት የስራ ቀናት አዲስ አበባ ሜክሲኮ የቀድሞ ሚቴክ ህንፃ ላይ በሚገኘው መስሪያ ቤታችን ግዥ ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ከታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ግዢ ክፍል ቢሮ ቁጥር 305 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤታችን ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 305 ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡– 01-15-31-00-19 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ጠቅላይ መምሪያ