በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የተለያዩ ጽሕፈት ዕቃዎችን፣ የተለያዩ ፈርኒቸር እና የተዘጋጁ አልባሳትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የተለያዩ ጽሕፈት ዕቃዎችን፣ የተለያዩ ፈርኒቸር እና የተዘጋጁ አልባሳትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት

 • የተለያዩ ጽሕፈት ዕቃዎችን፣
 • የተለያዩ ፈርኒቸር እና
 • የተዘጋጁ አልባሳትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው 

 1.  ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው፣
 2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
 3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
 4. የግብር ከፋይ ምዝገባ (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፤
 5. የዘመኑ ግብር የከፈለ /ከኢትዮ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠው የምስክር ወረቀት/ክሪላንስ/ማቅረብ የሚችል፣
 6. ተወካይ ከሆነ/ከሆነች/ ሕጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት:: 
 7. ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያው የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መኖር አለበት::
 8. . በዘርፉ ድምር ከተሰራ በኋላ የቫት ድምርም ለብቻው ማስቀመጥ አለበት: ተጫራች የአንዱን ዋጋ ቫት ሳይጨምር ለብቻው ማስቀመጥ አለበት:: 
 9. ተጫራች የአንድ ዋጋ ከሞላ በኋላ የጠቅላላ ድምር ወደ ጎንም ወደታችም ደምሮ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡ 
 10. በጨረታ አሸናፊ የሚሰየሙ በተቀመጠው የዕቃ ዝርዝር በተናጠል ዕቃ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው አሸናፊ ይሆናል፡፡ 
 11. በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም በተጨማሪ በሰነዱ ላይ ፍሉድ ካለው ሰነዱ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡ 
 12. ተጫራቾቹ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦሪጅናልና ኮፒ ብለው መለየት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጅናሉን ፋይናንሻል ለብቻ ኮፒውን ለብቻ በማሽግ እንዲሁም ከተራ ቁጥር ከ1-6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሽግና በመጨረሻ ሦስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ አሽጎ ኦርጅናል ብሎ ማቅረብ አለበት፡፡ስለሆነም በዚህ መሠረት ሦስቱንም ፖስታዎች ሳያሽግ በአንድ ላይ አሽጎ ቢመጣ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡ 
 13. ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም የክፍያ ማዘዣ በCPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡ 
 14. ተጫራቹ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን በትክክል አሽጎ ማቅረብ አለበት በሰም ያለማሽግ ከውድድር ውጪ አያደርግም:: 
 15. በጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ውል ሲይዝ ለውሉ ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በCPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
 16. ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከማሰልጠኛ ት/ቤቱ ፋይናንስ ዴስክ በሥራ ቀንና ሰዓት ከ24/7/2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 3/8/2012ዓ.ም ድረስ የሚጫረትበትን የመጫረቻ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላል፡፡ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ መታወቂያ ብቻ ይዘው በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ 
 17.  ተጫራች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በ14/8/2012ዓ.ም ከ2፡00 እስከ 7፡ 30 ሰዓት ድረስ በማ/ት/ቤቱ ቢሮ በር ላይ በሚዘጋጀው ሳጥን ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ።
 18. ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በማ/ት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ጨረታው በተዘጋበት ቀን በ14/8/2012 ዓ.ም ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡ 
 19.  አሸናፊ የሆነው ተጫራች ማ/ት/ቤቱ በሚሰጠው የአቅርቦት ትዕዛዝ መሠረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ እና በማነት/ ቤቱ ጥራት ኮሚቴ ተረጋግጦ ካልተቀበለው ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት:: 
 20. አሸናፊ የሆነው ነጋዴ ክፍያ በሚጠይቅበት ሰዓት ሕጋዊ ደረሰኝ ከካሽ ሪጅስተር ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡ ይህን ማቅረብ የማይችል ከሆነ ምንም ዓይነት ክፍያ መጠየቅ አይችልም:: ማ/ት/ቤቱም እንዲከፍል አይገደድም:: 
 21. ማ/ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
 22. ጨረታውን አሸናፊ ከሆነ ድርጅት ማ/ት/ቤቱ በጀቱን በማረጋገጥ በዘርፉ _20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
 23. ከላይ የተዘረዘሩት በሙሉ በሀገሪቱ የግዥ አፈፃፀም መምሪያ መሠረት ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡
 24. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር፡- 0587600018 በሥራ ሰዓት ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላሉ፡፡ 

ብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ት/ቤት