ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በምዕ/ዕዝ የ12ኛ መተማ ክ/ጦር ጠቅላይ መምሪያ ለ2013 ዓ/ም በጀት ዓመት ለክ/ጦራችን አገልግሎት የሚውሉ፡
- የቢሮ ፅህፈት መሳሪያ
- የሥልጠናና የት/ት መርጃ ፅህፈት መሳሪያ
- የቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ማቴሪያሎች
- የቢሮ ፅዳት ማቴሪያሎች
- የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች
- አላቂ የጋራዥ ጥገና ማቴሪያሎች
- ፕላንትና ማሽነሪ ማቴሪያሎች
- የተለያዩ የእጅ መገልገያ ማቴሪያሎች
- የተለያዩ አልባሳቶች
- የካቤክ የግንባታ ማቴሪያሎች
- የተለያዩ ፈርኒቸሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘመኑ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ ከብር 50,0000 ( ሃምሳ ሺህ ብር ) በላይ ለሚወዳደሩ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰርተፍኬት እንዲሁም ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን ግብር መክፈሉንና በጨረታ እንዲሳተፉ የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 ብር አንድ መቶ ብር ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ጅማ 12ኛ መተማ ክ/ጦር ጠቅላይ መምሪያ ግዥ ክፍል ጅማ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ምዕራብ ዕዝ ካምፕ ተብሎ በሚጠራው ግቢ ውስጥ በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
የማስረከቢያ ቦታ፡– ጅማ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት ዕቃዎች CPO ማስያዝ የሚችል
ጨረታው 30/1/2013 ዓ/ም እስከ 14/02/2013 ዓ/ም ድረስ በአየር ላይ ከዋለ በኋላ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3.00 ሰዓት ተዘግቶ በ14/2/ 2013 ዓ/ም ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሶሳ 12ኛ መተማ ክ/ጦር ጠቅላይ መምሪያ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12ኛ መተማ ክ/ጦር ጠቅላይ መምሪያ ጅማ
ስ.ቁ 0910851849/ 0960703420/ 0472118506
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በምዕ/ዕዝ የ12ኛ እግረኛ
ክ/ጦር መምሪያ