Water Engineering Machinery and Equipment / Water Pipes and Fittings / Water Proofing Works / Water System Installation

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ሠላም ማስከበር ማዕከል በ2013 በጀት ዓመት ሁርሶ በሚገኘው ቋሚ የሰራዊት ካምፕ ውሥጥ የውጭ የውሃ መስመር ዝርጋታ ብቁ ከሆኑ ተወዳዳሪዎች በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

 የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ግልጽ ጨረታ ቁጥር 002/2013

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ሠላም ማስከበር ማዕከል ከድሬዳዋ በስተምዕራብ 27 /ሜትር ላይ የሚገኘው የኮንቲንጀንት ማሰልጠኛት/ቤት(ካምፕ) 2013 በጀት ዓመት ሁርሶ በሚገኘው ቋሚ የሰራዊት ካምፕ ውሥጥ የውጭ የውሃ መስመር ዝርጋታ ብቁ ከሆኑ ተወዳዳሪዎች በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች በተገለፀው ዘርፍ መመዘኛ የምታሟሉ ብቃት ያላችሁ ተወዳዳሪዎች በግልጽ ጨረታ መወዳደር የምትችሉ መሆኑ ማሰልጠኛ /ቤቱ በደስታ ይጋብዛል፡፡

ሥራው፡ሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት(ካምፕ) የውጭ የውሃ መስመር ዝርጋታ እና ተያያዥ ግንባታዎች

ስስሆነም በጨረታው ስመሳተፍ የምትፈልጉ ኮንትራክተሮች፡-

 1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
 2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (Valve added tax) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
 3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
 4.  በኮንስትራክሽን ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ያላቸው፡፡
 5. በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጨረታ ላይ እንዳይሳተፉ ያልታገዱ እና በመንግስት የኮንስትራክሽን ስራ የግልጽ ጨረታ አፈፃፀም መመሪያ መስፈርት መሠረት ለመወዳደር ብቁ የሆኑ፡፡
 6. በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ WCGC ደረጃቸው 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑና  አምስት ዓመት ተከታታይ የሠሩትን የኦዲት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ በየትኛውም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ህጋዊ ውል ገብተው ያለስራ ጥራት ጉድለት ያጠናቀቁ፡፡
 7. 2008 . ጀምረው ባለው ጊዜ ውስጥ በተመሳሳይ ስራ አሽንፈው ያጠናቀቁት ኘሮጀክቶች በዝርዝርና ከነመልካም ስራ አፈፃፀም ሰርተፍኬታቸው አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 8. የስራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን (ቴክኒክ) ብቃት መወዳደሪያ ሰነዶች  ዋና (ኦርጅናል) ኮፒ ሲጠየቁ አቅርቦ ማመሳከር አለባቸው ይህ ተጣርቶ ኮፒ  ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
 9. ማንኛውንም ተጫራች የመወዳደሪያ ዋጋ ሊሞሉ ከተእታ ስፊት ያለ የነጠላ ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
 10.  ቴክኒካል ውድድሩን ያላለፈ ተጫራች ፋይናንሽያሉ ሠነድ አይከፈትም፡፡
 11. የጨረታ ማስከበሪያ unconditional Bank Guarantee ወይም የክፍያ ማዘዣ CPO 180,000.00 (አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 12. የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ቢድ ቦንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው፣ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ በሁሉም ዶክሜንት ላይ ህጋዊ የሆነ የድርጅቱ ባለቤት ፊርማና ማህተም መደረግ አለበት፡፡
 13. ተጫራቾች ጨረታውን ያሸነፉ እና አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ ካሟሉ በኋላ የግንባታ መሣሪያዎቻቸውን በቦታው አጓጉዘው ማድረስ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
 14.  ተጫራቾች ማጭበርበር፣ ሙስና እና ማታለልን በተመለከተ ላለመፈፀም በኢትዮጵያ ህጐች የተደነገገውን የሚያከብር እና የሚያስከብር መሆን አለበት፡፡
 15. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች የጨረታው ውጪ ይደረጋሉ፡፡
 16. አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ  7 ቀናት በኋላ ለውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ካሸነፉበት ዋጋ 10% conditional Bank Guarantee ወይም (CPO) አሰርተው ውል መዋዋል ይኖርበታል ፡፡
 17. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞሉ በጨረታ ሰነዱ በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
 18. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ማድረግ፣ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል፣ ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
 19. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ማስረጃ (ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ (ፍሉድ) ካለበት ከጨረታ ውጪ ይሆናል::
 20. ለጨረታ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 90 ቀናት የማይቀየር (የፀና) ይሆናል፡፡

ጨረታ የሚከፈትበትና የሚዘጋበት ቀን፡-

21 በኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ /ቤቱ የሚከናወነው የግልጽ ጨረታ ከጠዋቱ 200 እስከ 815 ሰዓት ዋጋው የተሞላው ሰነድ ታሽጎ ወደ ተዘጋጀለት የጨረታ ሳጥን በ1/4/2013 . 815 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ /ቤቱ (ሁርሶ)  የመሰብሰቢያ አዳራሽ ቁጥር 19 በ1/4/2013 . ይከፈታል:: ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን 10/3/2013 . ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን 1/4/2013 . ድረስ ለዚሁ ጨረታ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ :

22. በአዲስ አበባ እና ዙሪያ የምትገኙ ተወዳዳሪዎች ጃንሜዳ በመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል ግዥ ድን ስልክ ቁጥር 0913 31 63 48 በመሄድና እንዲሁም ከሠላም ማስከበር ማእከል ፋይናንስ ቡድን የሰነድ ከፍያ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

23. በድሬዳዋ እና ዙሪያ የምትገኙ ተወዳዳሪዎች በሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ /ቤት ግዥ ዴስከ ቢሮ ቁጥ 26 ስልክ ቁጥር 025 447 0115 ነዱ በመውሰድና ፋይናንስ ዴስክ የሰነ ክፍያ በመክፈል 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል የከፈሉበትን ህጋዊ ደረሰኝ በማሳየት ሀርድ ኮፒ መውሰድ ይችላሉ፡፡

24.መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ፡-

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል

ሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ /ቤት

ስልክ ቁጥር፡-0254470115

በመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል

የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ /ቤት

ሁርሶ