የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡ትራ/መም/ግ001/2013A
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ህ/ሎጅ/ዋ/መም/የትራ/መም/ግዥ ዴስክ በ2013 የበጀት አመት የከባድ ተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል ::
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ እና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣
- የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ፧
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ብር 58,502.00/ ሃምሳ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሁለት ብር /ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ በCPO ማስያዝ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 150.00/አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት ላሉ ፧
- የጨረታው ማስታወቂያ ታትሞ ከወጣበት ቀን በ16ኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ::
- የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች የሚያቀርቡት ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታው ሰነድ የሚላከው በአካል ቢሮው ድረስ በመምጣት ሲሆን ለሚዘገይ የጨረታ ሰነድ ኃላፊነት የማንወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ላሸነፉባቸው ዕቃዎች ለውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ካሸነፈው ዋጋ ላይ 10% በCPO ማስያዝ ይኖርበታል ::
- መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለማብራሪያ እና የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ የሚያገለግል አድራሻ
ሀ. ትራንስፖርት መምሪያ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ የድሮ መኮድ አጠገብ
ስልክ ቁጥር 011-434-58-65/0114341600
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ህ/ሎጅ/
ዋ/መም/ የትራ/መምሪያ ግዥ ዴስከ