በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዲያ ዞን የአመካ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለሁሉም ሴ/መ/ቤቶች የጽህፈት መሣሪያ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ወይንም ኣቅራቢዎች ማለትም፡-
- በመስመሩ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2013 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፡፡
- የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- ቫት ተመዝጋቢ የሆነና
- Tin no (የግብር ከፋይነት ቁጥር ) ያላቸው ሆኖ
- የጨረታ ሰነድ ከእመካ ወረዳ ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7,000 (ሰባት ሺህ ብር) ብቻ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይንም ካሽ ከጨረታ ሰነድ ጋር ይዞ መቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ታከስን የሚያካትት መሆኑን መገለጽ አለበት ታክስ በትክክል ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ታክስን እንዳካተታ ተደርጎ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡
- የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን በፖስታ አሽገው የድርጅቱን ስም፣ ማህተምና ስልክ ቁጥር መጻፍ አለበት፡፡
- ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ሥራ ቀናት እስከ 15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ15ኛው ቀን በ4፡10 ሰዓት ታሽጎ በ4፡20 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡
- ከጨረታ መዝጊያ ጊዜ በኋላ ዘገይቶ የመጣ ኤንቨሎፕ ተቀባይነት አይኖረውም እንደታሸገ ለተጫረቹ ይመለሳል፡፡
- በጨረታ ለተሸነፉት ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት cpo ወይንም ብር አሸናፊ ከተለያ በኋላ ይሰጣቸዋል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በነጠላ ዋጋ/unit price/ ወይንም በነጠላ ዋጋ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ሲሆን ተጫራቾቹ በሁሉም ዕቃዎች ቢወዳደሩ የተሻለ ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉበትን ዕቃ በራሱ ወጪ እስከ አመካ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት አቅርቦ ማስረከብ የሚችል፡፡
- አሸናፊ ከሆኑ የዕቃዎችን ናሙና ማቅረብ የሚችል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0945-90-94-95 ደውለው መረዳት የምችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የአመካ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
(ጌጃ)