የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር የመኪና አካል ጥገና አገልግሎት ዕቃ ግዢ HUDO/NCB/01/01/2013 BY
የግዥ መለያ ቁጥር ቢሮ የጽሕፈት መሣሪያ ዕቃ ግዥ ዘUDC/NCB/01/03/2013 BY
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዳዬ ካምፓስ ለ2013 በጀት ዓመት
- ለካምፓሱ መኪናዎች የአካል ጥገና አገልግሎት ግዥ እና
- ለተለያዩ ቢሮ መገልገያ የሚሆን የጽሕፈት መሣሪያ ግዥ ለመፈጸም እንዲያስችለው አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መምረጥ ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግስት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልፁ ማስረጃ፣በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ የመረጃ መረብ ድህረ ገጽ/webisite/ ላይ የተመዘገቡ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ )የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር ለመኪና አካል ጥገና አገልግሎት ግዥ እና 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ለጽሕፈት መሣሪያ ግዥ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ፣ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የጨረታው ሳጥን ከመከፈቱ በፊት የተዘጋጀው ማቅረብና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታውን ለመካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 50 ብር (ሃምሳ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከዳዬ ካምፓስ ከግዥና/ንብ/አስ/ቡድን መግዛት ይችላሉ ::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ክፍት ቦታ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ እስከ አስራ አምስተኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ሆኖ አስራ አምስተኛው ቀን ዕለቱ በዓል / ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ግን በቀጥታ ተከታይ የስራ ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላል፡፡
- ጨረታው በግልፅ የሚከፈተው በተ/ቁ አራት በተጠቀሰው በአስራ አምስተኛው ቀን በ11፡00 ታሽገው በአስራ ስድስተኛው ቀን /በማግስቱ/ በ3፡30 ሰዓት ሲሆን ዕለቱ በዓል ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ግን በቀጥታ ተከታይ የስራ ቀን 3፡30 ሰዓት የመክፈቻው ቦታ በሀዋሳ ዩነቨርሲቲ ዳዬ ካምፓስ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ በሚገኘው ቦታ ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ጨረታውን ካሸነፉ ውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ተሰልቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ቅድመ ክፍያ የሚፈልጉ ከሆነ በሚጠይቁት ልክ ተመጣጣኝ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ካምፓሱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ከግዥና ንብ/አስ/ቡድን ስልክ፡ 0949036813/ 0916316245
በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዳዉ ካምፓስ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን