የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ግብርና መምሪያ በ2013 በጀት ዓመት
- የተለያዩ የእንስሳት ጤና ግብአቶች ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የተሰማሩትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፣-
- የተለያዩ የእንስሳት መድሃኒቶች፣
- የህክምና መገልገያ ዕቃዎች፣
- የእንስሳት ክሊኒክ፣ የላቦራቶሪ ዕቃዎችና ኬሚካሎች ስለሚፈልግ የአንስሳት ጤና ግብአቶች አቅራቢ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ግብአቶች (መድሀኒቶች) 2 ዓመትና ከዚያ በላይ የመጠቀሚያ ጊዜ ያላቸው፡፡
- ግብአቶች (መድሀኒቶቹ) የስሪት አገርና ሰሪ ካምፓኒ በመጥቀስ የመወዳደሪያ ዋጋም በስሪት አገርና ሰሪ ካምፓኒ መሠረት ለያይቶ ማቅረብ አለበት፡፡
- በአን/መድ/መኖ አስ/ቁጥጥር ባስሥልጣን በተለያያ ምክንያት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የተከሰከሉ የእንስሳት ጤና ግብአቶች (መድሀኒቶች) ማቅረብ የለበትም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
- የጨረታ ሰነዱ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀናት ሥራ ሰዓት በመጠቀም ጨረታውን በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 (ግዥ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ እና የጨረታ ሰነድ የገዙበት ደረሰኝ አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው በ15 (አስራአምስት) ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል። ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ አንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-0462121334
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ
ሀዋሳ