የጨረታ ማስታወቂያ
ቅምብቢት ወረዳ ፍርድ ቤት በ2013 በጀት ዓመት የተለያዩ፡
- ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎች
- የህትመት መሳሪያ (pressing material) )
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች (Electronics material)
- ቋሚ የቢሮ እቃዎች (Furniture) አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በየስራ ዘርፉ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፤ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላችሁ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT 15% ተመዝጋቢ የሆናችሁ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላችሁ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በቅምብቢት ወረዳ ፍርድ/ቤት በግንባር በመቅረብ ዝርዝር መጠይቆችን የያዘውን ሰነድ በማይመለስ በብር 50 በካሽ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በካሽ ወይም ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ፡– እስከ 10/ 03/1213 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት በ10/3/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ማሳሰቢያ ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ውሉን ፈጽሞ እቃዎችን የማስገባት ግዴታ አለበት፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ:-ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 78 ኪሎ ሜትር ሸኖ ከተማ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0116870608 /0116870609 በመደወል ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን
የቅምብቢት ወረዳ ፍርድ/ቤት