የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2013 ዓ.ም
ሽርሽር አዲስ ትሬዲንግ ለ2013 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የተዘረዘሩትን ለቢሮ መገልገያና የስፌት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
- የስቴሽነሪ እቃዎች
- የጽዳት ዕቃዎች
- የደንብ ልብስ
- የስፌት አገልግሎት
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶችን መወዳደር ይችላሉ።
- በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያላቸው
- የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት
- የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- ከሃገር ውስጥ መስሪያ ቤት የጨረታ መሳተፊያ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ማስከበሪያ
- ለጽህፈት መሣሪያ ብር 20,000.00/ ሃያ ሺ ብር/
- ለጽዳት ዕቃዎች ብር 20,000.00 /ሃያ ሺ ብር/
- ለደንብ ልብስ ብር 15,000.00/ አስራ አምስት ሺ ብር/
- ለስፌት አገልግሎት ብር 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ ከሠነዱ ጋር በሽርሽር አዲስ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስም አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ብቻ ማቅረብ ሲገባቸው በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ አይቻልም።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምድብ የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 150/ አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጋዜጣው ከወጣበት አንስቶ ቦሌ ስናፕ ፕላዛ ሰባተኛ ፎቅ በመገኘት መግዛት ይችላሉ
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለሁሉም ምድቦች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
አድራሻ ቦሌ ስናፕ ፕላዛ ሰባተኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር +251 983 83 20 83
ሽርሽር አዲስ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር