ሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የህትመት ውጤቶችን (የጠረጴዛ ባጅ፣ ደረሰኞች፣ የሞተር ሳይክል ስቲከር እና ሌሎች) ይፈልጋል

Bid Closing Date: Aug 23, 2019 02:00 PM

የጨረታ ቁጥር SMTSE/ግጨ/ ህት/01/2012/2019 

ሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት

  • የህትመት ውጤቶችን (የጠረጴዛ ባጅ፣ ደረሰኞች፣ የሞተር ሳይክል ስቲከር እና ሌሎች) በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡

  1. ከሥራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ወቅታዊ ደብዳቤ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን (Tax- Clearance)፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በመንግሥት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት (VAT Registration) እና የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት (TIN Certificate) ማቅረብ አለበት፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመያዝ 22 እየሩስ ሕንፃ፣ 7ኛ ፎቅ፤ ሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የግዥና ንብ/አስተ/ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7-07 መውሰድ የሚችሉ ሆኖ የጨረታው ሰነድም በዚሁ አድራሻ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1 ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያው ከሕጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶች /ከቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል ጋር መቅረብ አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከወሰዳችሁበት ቀን ጀምሮ በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ እስከ ነሐሴ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ከ8፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ፡፡ የእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነድ ከላይ በተገለጸው ቀንና ቦታ ሆኖ ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ዘግይቶ የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
  6. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዳቸው ሎቶች የታሸገ አራት ኤንቨሎፕ (ኦርጅናል) ቴክኒካል ሰነድ፣ ኮፒ ቴክኒካል ሰነድ፣ ኦርጅናል ፋይናንሻል ሰነድ እና ኮፒ የፋይናንስ ሰነድ) ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን፣ ፖስታዎቹ ተለያይተው የቀረቡ ሆነው ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ፖስታዎቹ ላይ መገለጽ አለበት፡፡
  7. የሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  8. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-8-33-34-62/0118-33-4076 ጨረታውን የሚመለከቱ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

ሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት

አገልግሎት ድርጅት