የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/13
ስኳር ኮርፖሬሽን (ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ) ከዚህ በታች የተመለከቱትን ጭነቶች ለማጓጓዝ የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር እና ከአሸናፊው ጋር የውል ስምምነት በመፈጸም ማሠራት ይፈልጋል።
1 |
100,000 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ |
–ከአዲስ አበባ ወደ ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ –ከአዳማ ወደ ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ –ከነቀምት ወደ ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ |
2 |
5,000 ኩንታል ሲሚንቶ |
–ከአዲስ አበባ ወደ ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ –ከሙገር ወደ ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ |
3 |
3,000 ኩንታል አልሙኒየም ሳልፌት |
–ከአዋሽ መልካሳ ወደ ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ |
4 |
18,000 ኩንታል ትኩስ ኖራ |
–ከዝዋይ ወደ ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ |
5 |
1,000 ኩንታል ሀይድሬትድ ለይም |
–ከዝዋይ ወደ ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ |
6 |
የተለያዩ የአገር ውስጥ ግዥ ዕቃዎች በኩንታል |
–ከአዲስ አበባ ወደ ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ |
7 |
ባለ 40 ፊት ኮንቴነር የውጭ ግዥ |
–ከጂቡቲ ወደ ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ –ከሞጆ ወደ ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ |
8 |
ባለ 20 ፊት ኮንቴነር የውጭ ግዥ |
–ከጂቡቲ ወደ ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ –ከሞጆ ወደ ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ |
9 |
ባለ 40 እና ባለ 20 ፊት ባዶ ኮንቴነር |
–ከፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ ወደ ጅቡቲ –ከፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ ወደ ሞጆ |
ስለዚህ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ጨረታውን ለመግዛት ማመልከቻ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የኣቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፊኬት በማቅረብ እና የማይመለስ ብር 100.00 (ብር አንድ መቶ) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚከተለው አድራሻ በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
የግዥ ዋና ክፍል
ሜክሲኮ፣ ፊሊፕስ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 209
የስልክ ቁጥር 011-5513706
የፋክስ ቁጥር 011-551-29-11
2. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፊኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000 (ብር ሃያ አምስት ሺህ) በሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው፣
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ተከታታይ ቀናት 8:00 ሰዓት ከመሆኑ በፊት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
4. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን 8፡15 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 205 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ የማስገቢያውም ሆነ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከናወናል።
5.ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስኳር ኮርፖሬሽን(ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ)