የተለያዩ የቢሮ ማሽን የአገልግሎት ግዢ
በድጋሚ የወጣ ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር LP/OT/09/SC/2013
ስኳር ኮርፖሬሽን የተለያዩ ዓይነት የፎቶ ኮፒ፣ ፕሪንተር፣ ፋክስ፣ ስካነር እና ዩፒኤስ ባትሪዎች የጥገና አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1.በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የ2012/2013 ዓ.ም በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
2. ጨረታው ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት ላይ ይክፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በተራ ቁ. 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ጨረታው የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው፡፡
ስኳር ኮርፖሬሽን ግዥና ሎጀስቲክስ
ካሳንቺስ ፣ ከንግድ ሚኒስቴር በስተቀኝ ገባ ብሎ
ኪያሜድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ጀርባ ባለው አዲሱ ሕንፃ 4ኛ ፎቅ
ጆሴፍ ቲቶ መንገድ
ስልክ ቁጥር 0115500569
ፋክስ ቁጥር 015158030
አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ
5.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (ብር አስር ሺ)፣ በሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረታ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡
7.የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የመቆያ ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው፡፡
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስኳር ኮርፖሬሽን