ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር LP/OT/13/SC/2013
ስኳር ኮርፖሬሸን ከተለያዩ ስኳር ፋብሪካዎች ወደ አዲስ አበባ እና አዳማ ከተማ የኮርፖሬሽን መጋዘኖች ስኳር ለማጓጓዝ የትራንስፖርት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2012/13 ዓ.ም. የታደሰ/አዲስ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው
- ጨረታው ጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል:: ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቀጥሎ በቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ ጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ብር ሁለት መቶ) በመክፈል ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
ስኳር ኮርፖሬሽን
ግዥና ሎጅስቲክስ
ካሳንቺስ፣ ከንግድ ሚኒስቴር በስተቀኝ ገባ ብሎ
ኪያሜድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ህንፃ 4ኛ ፎቅ፣ ከነባሩ ቢሮ በስተጀርባ
ቢሮ ቁጥር 102
ጆሴፍ ቲቶ መንገድ
ስልከ ቁጥር 0115500569
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺህ) በሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5 ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው፡፡
7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሰሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስኳር ኮርፖሬሽን