በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ስካይ ባስ ት/ሲ/አ ማህበር በድጋሚ ለጨረታ የቀረቡ ሦስት አገልግሎት
- የሰጡ አውቶቡሶችንና በተጨማሪም ያገለገሉ መለዋወጫዎችንና ብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የተጠቀሱት ንብረቶች በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 720 በማህበሩ ጋራዥ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን መግዛት የሚፈልግ ተጫራች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ከፍሎ የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመውሰድና ንብረቶቹን በማየት የሚገዛበትን ዋጋ ሞልቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የሥራ ቀናት ውስጥ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 068 ቄራ አካባቢ መላቅ ትሬዲንግ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ በድርጅቱ ቢሮ ማቅረብ ይችላል፡፡ ጨረታው በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታ ሣጥኑ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ከቀኑ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ስካይ ባስ ት/ሲ/አ/ማህበር